በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሊሆን የማይገባውን “ የዘር ማጥፋት ዘመቻን የሚደግፉ የሶስተኛ ወገን ሀገራት አሉ ተባለ

የኮሎምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊስ ጊልቤርቶ ሙሪሎ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ፈፅሞ መሆን የሌለበትን የዘር ማጥፋት ዘመቻን በግልጽ የሚደግፉ የሶስተኛ ወገን ሀገራት አሉ ብለዋል።

ሙሪሎ በዶሃ የውይይት መድረክ ላይ በጋዛ ስላለው ችግር ለሃገራት መሪዎችን ተችተዋል ።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እየተባባሰ የመጣውን የጋዛ ብጥብጥ መፍታት አለመቻሉ ያሳዝናል ያሉት ሚሲትሩ ይህ ተግባር ‘የዘር ማጥፋት ወንጀል’ ነው ሲሉም ነቅፈዋል።

ይሁን እና ሚኒስትሩ በጋዛ ያለውን ሁኔታ በግልፅ እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራትን ጨምሮ ሌሎች የዘር ማጥፋት ዘመቻውን የሚደግፉት የሶስተኛ ወገን ሀገራት መንግስታት ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

ልዑል ወልዴ

ታኅሣሥ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *