English Primer League Matchweek 16

ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ቼልሲ ኢና ቶተንሀም ጣፋጭ ድል ተቀዳጅተዋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ  መርሐግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አማድ ዲያሎ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ ሲያሳርፉ ለማንችስተር ሲቲ ቫርዲዮል አስቆጥሯል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከአሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ የመጀመሪያ የማንችስተር ደርቢ ጨዋታቸውን ያሸነፉ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆነዋል።

ማንችስተር ሲቲ ካለፉት አስራ አንድ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው።

ቼልሲ ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሰማያዊዎቹን የድል ግቦች ኒኮላስ ጃክሰን እና ኩኩሬላ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ ከፕርሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችለዋል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች ሰባት የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

ቶተንሀም ከሳውዝሀምፕተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ጄምስ ማዲሰን 2x ፣ ሰን ፣ ኩሉሴቭስኪ እና ፓፔ ሳር ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ሰን ሁንግ ሚን በፕርሚየር ሊጉ የቶተንሀም የምንግዜም ብዙ አመቻችቶ ማቀበል የቻለችው (68) ተጨዋች መሆን ችሏል።

የሊጉ ደረጃቸው

1 ሊቨርፑል :- 36 ነጥብ
2  ቼልሲ :- 34 ነጥብ
3 አርሰናል :-30 ነጥብ
4 ኖቲንግሀም ፎረስት  :- 28 ነጥብ
5  ማንችስተር ሲቲ :- 27 ነጥብ
10  ቶተንሀም :- 23 ነጥብ
12 ማንችስተር ዩናይትድ :- 22 ነጥብ

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *