“ኑ ቤታችንን እንስራ ” ብሏል ጌርጌሴሮን የአእምሮ ህመማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል

ላለፉት 19 አመታት የአእምሮ ህመማንን ሲረዳ የቆየው ጌርጌሴሮን የአእምሮ ህመማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ከጊዜ ወደ ጊዜ የህሙማኑ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከፍተኛ የቦታ ጥበት እንደገጠመው የማዕከሉ መስራች ሊቀ ህሩያን መለስ ገልጸዋል፡፡

ይህንን የቦታ ጥበት የተመለከተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦታ ድጋፍ በማደረጉ ጊዜያዊ መጠለያ በመስራት የህንጻ ግንባታ ቢጀምርም ከፍተኛ የሆነ የግንባታ እቃዎች መወደድ እና የአቅም ማነስ ተዳምሩ ስራዎችን በፍጥነት መስራት እንዳቃታቸው ተናረዋል፡፡

ሊቀ ህሩያን መለስ ማዕከሉ በዚህ ሰአት 700 የሚደርሱ የአእምሮ ህመማን ተቀብሎ መጠለያና ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ገልጸው አዲሱ ህንጻ ተገንብቱ ሲጠናቅቅ ድጋፍ የሚሰጣቸውን ህሙማን ቁጥር ወደ 5000 ለማሳደግ እቅድ አለን ብለዋል፡፡ ይሄንን ለማሳካት መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

ለጌርጌሴሮን የአእምሮ ህመማን #መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ ማድረግ ለምትሹ

በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000649044183

በአቢሲኒያ ባንክ 1219 ወይም 1998

ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1026600059494

በቴሌ ብር 500464 መጠቀም ትችላላችሁ

አፎሚያ አሸናፊ

ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *