የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት “የመገናኛ ብዙሃን ሚና በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ በማቅረብ የአጀንዳ ልየታ ለማድረግ ከመገናኛ ብዙሃን ከተወከሉ ባለሞያዎች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት ጀምሯል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽር (ዶ/ር) ተገኘ ወርቅ ጌቱ ባደረጉት ንግግር በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው የአጀንዳ ልየታ እንደተጠናቀቀ ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ውጪ በሌሉች ክልሎች እንደሚካሄድ ጠቅሰው፡፡በሁለቱ አካበቢዎች ግን ምቹ ሆኒታ እንደተፈጠረ ወዲያው ወደ ተግባር ይገባል ብለዋል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን በተለይ እንዲህ ባሉት ሀገራዊ ጥቅችን በሚያስጠብቁ ሆነቱች ላይ አይነተኛ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባልም ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ አካታችና አሳታፊ እንዲሆን መገናኛ ብዙሃን የምክክሩን አስፈላጊነትና ምንነት ላይ ግንዛቤ በመፍጠር እያደረጉ ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል።
በቀጣይም ብሔራዊና የህዝብ ጥቅምን በማስቀደም ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ሊቀመንበር አቶ አማረ አረጋዊ ‹‹ ሚዲያው በብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፡፡ ከምንም በላይ ግን ከውጤቱ የበለጠ አካሄዱ ላይ ጥንቃቂ እና ሙያዊ ስምግባር በጠበቀ መልኩ ስራዎች መሰራት ይገባል ብለዋል፡፡
በየደረጃው ያሉ አካላትም ጋዜጤኞች ከስጋት እና ከፍረሃት ነፃ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይህ የምክክር መድረክ በነገው እለትም እንደሚቀጥል ከአዘጋጁቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
