በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሚከበረው አመታዊ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የፀጥታ ዝግጅት ማደረጉን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያዉ የሚዲያ ገፅታና ግንባታ ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስፔክተር ዳግም ተፈራ ለኢትዬ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከተለያዩ የምስራቅ ቀጠና ከሚገኙ አጎራባች ክልሎች እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ ፣ሚኒሻን ጨምሮ ከምስራቅ ሀረርጌ ፖሊስ ጋር በጋራ ዉይይት በማድረግ ከእቅድ እስከ ስምሪት
ለበዓሉ አስፈላጊው የዝግጅት ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል
የአገልግሎት ሰጪ ተቆማት በበቂ መልኩ ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ እና የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ኢንስፔክተር ዳግም አስታውቀዋል
የበአሉ ታዳሚያን ወደ ከተማዉ በሚገቡበት ጊዜ በከተማው ከንቲባ እና ፖሊስ ኮሚሽነር የተመራ ቡድን እንግዶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርጉ ተነግሯል ፡፡
ለበዓሉ ወደ ድሬዳዋና ቁልቢ የሚመጡ ምዕመናን ያለምንም ሃሣብ ወደ ስፍራው በመምጣት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
አቤል እስጢፋኖስ
ታኀሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
