ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ሸሪዓን መሰረት ያደረገ የዲጂታል ፋይናንሲንግ አገልግሎት አቅርቧል።
ይህ ስያሜው “አንሳር” የተባለው አዲስ ዲጂታል ፋይናንሲንግ አገልግሎት፤ ያለማስያዣ በስልክ ብቻ ለሰፊው ማሀበረሰብ መድረስ የሚችል የፋይናንሲንግ አገልግሎት ሲሆን ዘምዘም ባንክ ከክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ጋር በመሆን ያዘጋጀው መሆኑም ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል አቶ ሰለሞን ደስታ በኩላቸው ዘምዘም ባንክ ይፋ ያደረገው ይህ የዲጂታል ፋይናንሲንግ አገልግሎት ብሄራዊ ባንክ የያዘውን የአካታችነት መርህ ተግባራዊ ያደረገ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ለሴቶች ፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም ለሰፊው ማሀበረሰብ እንዳቀረበም ተገልጿል።
የፋይናንስ አገልግሎት በተመጣጣኝ ሁኔታ የቀረበ መሆኑም ተመላክቷል።
ለዓለም አሰፋ
ታኀሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
