ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ

መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የሚሰራው በጎ ስራ ነውና፤ ሁሉም በአቅሙ ሊደግፈው እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ባደረጎት ንግግር አሳስበዋል፡፡

የመቄዶኒያ አረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከስምንት ሺህ በላይ የሚሆኑ አረጋውያንና አዕምሮ ህሙማንን እየረዳና እየተንከባከበ ይገኛል።

በአሁኑ ጊዜ የማዕከሉ የቀን ወጪ ከሁለት ሚሊዮን ብር መሻገሩ ተገልጿል።

መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በ44 ከተሞች ከ8 ሺህ በላይ አረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማንን እየደገፈ ያለ ሲሆን፤ በቀጣይ ይህን ቁጥር ወደ 20 ሺህ ለማድረስ እየሰራ ይገኛል።

አፎሚያ አሸናፊ

ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *