ማስተር ሄኖክ 90 ቀናት ሁለንተናዊ ለውጥ ማዕከልና፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛና ፖርኮች ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው ዕለት ተፈራረሞዋል።
የዚህ ዝግጅት ማስጀመሪያም ታላቁ የኢትዮጲያ የተራራ ጉዞ (ሀይኪንግ) ውድድርና ፌስቲቫል ከ10.000 በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት ልዩ ዝግጅት ጥር 25 /2017 ዓ.ም በእንጦጦ ፖርክ በጋራ ያከናውናሉ።
በዝግጀቱ የአዲስ አበባ ከተማና አካባው ነዋሪ ስፖርተኞች፤ ታዋቂ ስዎች ፤የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።
የመግባቢያ ሰነዱ ማስተር ሄኖክ 90 ቀናት ሁለንተናዊ ለውጥ ማእከል ሰዎች ከዉፍረትና ከዉፍረት ጋር ተያይዘው ከሚመጡ በሽታዎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ንቁ፤ ብርቱ፤ ጀግና በሚል ልዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በወዳጅነት ፓርክ ለ 90 ቀናት ከ 1000 በላይ ሰዎች የእካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና ላይ ይገኛሉ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የስነ ምግብ ባለሙያ በሆነው ማስተር ሄኖክ ኪዳነወልድ የሚመራው በ90 ቀናት ሁለንተናዊ ለውጥ ማእከል ባለፉት አስር አመታት በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የሀይወት ክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት የሚታወቅ ተቀም ሲሆን በአሁኑ ሰአት በሃገራችን አየተለመደ ለመጠው የማስ ስፖርትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አብዮት ተቀሙ ግንባር ቀደም በመሆን 1000 ሰዎችን በነጻ አሰልጥኖ የጨረሰ ሲሆን ቀጣይ 2000 ነጻ ሰልጣኞችን ለመቀበል ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
