በጋምቤላ ክልል ወርቅ ለማወጣት የውሃ እጥረት መሰናክል ሆኗል።

በክልሉ የሚገኙ የወርቅ አዉጪዎች  ከፍተኛ የዉሃ እጥረት እንደገጠማቸው ተሰምቷል።

በተለይም የበጋ ወቅትን ተከትሎ በወርቅ ማዉጪ አካባቢዎች ዉሃ አለመኖር በስራቸው ላይ ችግር እንደፈጠረ ሰምተናል።

በክልሉ የወርቅ ማዉጣት ላይ ተሰማርተው ያሉ አምራቾች ችግሩ ለስራቸዉ እንቅፋት እንደሆነባቸዉም ተገልፆል።

የጋምቤላ ክልል የማእድን ልማት ቢሮ የፍቃድ አሰጣጥ ዘርፍ ባለሙያ አቶ ሙት ሎንግ ይህ የዉሃ እጥረት የምርት ብክለት እንዲኖር ስለማድረጉ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በወርቅ ማዉጣት ሂደቱ ላይ ከፍተኛ የዉሃ ፍላጎት እንደሚኖር  ተነስቷል።

ሆኖም  የዉሃ አለመኖር በስራ ወቅት ወርቅን  ከአፈር ለማላቀቅ እንዳይቻል እና አስቸጋሪ እንዳደረገዉ አቶ ሙት ሎንግ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ለወርቅ ቁፋሮ ሥራ የሚያገለግሉ ማሽነሪዎች ለማስገባት አመቺ የመንገድ የመሰረተ ልማት አለመኖር በአምራቾች ዘንድ ሌላዉ እንደ ችግር እየተነሳ መሆኑን አያይዘዉ አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ የወርቅ አወጣጥ ስርአቱን እንዲሁም ጥራቱን ለመጠበቅ በቴክኖሎጂ በመደገፍ እየተሰራ መሆኑን አቶ ሙት ሎንግ አያይዘዉ ገልፀዋል።

የወርቅ ምርት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ቁልፍ ሚና ከሚጫወቱ የኤክስፖርት ምርቶች መካከል አንዱ ሲሆን የወርቅ ጥራት ጉድለት የገቢ መቀነስ ከሚያስከትሉ ችግሮች ዉስጥ ይቀመጣል።

ቁምነገር አየለ

ታኀሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *