ገዳ ባንክ በዛሬዉ እለት በዋና መስሪያ ቤቱ የባንኩን ሁለተኛ አመት ዝግጅት አክብሯል፡፡
ባንኩ የተመሠረተበትን ሁለተኛ አመት እያከበረ ባለበት ወቅት ሁለት የዲጂታል ፋይናንስ መተግበሪያዎችን ስራ እንደሚያስጀምር አስታዉቋል።
እነዚህን አዳዲስ የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቶች የባንኩ ሀላፊዎች እንዲሁም የቅርንጫፍ አመራሮች አስተዋዉቋል።
የባንኩ ደንበኞችን ፍላጎት ለሟሟላት ያስችላል የተባለው የባንኩ የሞባይል አፕሊኬሽን የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል መሆኑን ተገልፆል።
ከዚህ ዉስጥ የኢትዩጵያ አየር መንገድ የጉዞ ክፍያዎችን ጨምሮ ወደ ሌሎች ባንኮች ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲሁም የሞባይል የአየር ሰአት መሙላት የሚያስችሉ የአገልግሎት ይዘቶች ያሉት ነዉ ተብሏል።
በዚህ በቅርቡ ይፋ በሚደረገዉ የሞባይል አኘ መተግበሪያ የባንኩ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችን እና የኤት ኤም ቦታዎች ማሳየት የሚችል መጠቆሚያ ማካተቱን የባንኩ አመራሮች ገልፀዋል።
ደንበኞችን ዘመኑን ከሚጠይቁ የዲጂታል ፋይናንስ አሰራሮች ጋር ለማስተዋወቅም የሚያስችሉ ስራዎች በቀጣይነት እንደ እቅድ መያዙን ባንኩ ተናግሯል።
ባንኩ 42 ሺ 930 የሚሆኑ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ማፍራት መቻሉን የባለ አክሲዮኖች ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ገልፆ ነበር፡፡
የገዳ ባንክ በሁለት አመታት ዉስጥ ቅርንጫፎቹን 90 ማድረሱን ያስታወቀ ሲሆን በዚህም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎቹን በማስፋት በ2016 ሬ አመት በመቀሌ ከተማ አዲስ ቅርንጫፍ መክፈቱ አስታውሷል፡፡
ባንኩ የደንበኞቹን ቁጥሩንም ወደ 2 መቶ 88 ሺ 174 ከፍ ማድረጉ ተገልፆል፡፡
ቁምነገር አየለ
ታኀሣሥ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
