ከአዲስ አበባ በ350 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ጅማ ከተማ ሀይሌ ሆቴል 10ኛ መዳረሻውን ለአገልግሎቱ ክፍት አድርጓል።
በጅማ ከተማ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የሀይሌ ሆቴል ከ1.7ቢሊየን ቢሊየን ብር በላይ መፍጀቱ ተገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የኮንስትራክሽን እቃዎች ውድነት ቢፈትነንም ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ ችለናል ብለዋል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሂር ባደረጉት ንግግር የዚህ ሆቴል መመረቅ በጅማ ዞን እና ከተማ ተቀዛቅዞ የቆየውን የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዳግም ህይወት የሚዘራበት ነው ብለዋል።
ሆቴሉ 107 ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 92 ስታንዳርድ ሲሆኑ ወደ 5መቶ የሚጠጉ ሰዎችን መያዝ የሚችል የመሰብሰቢያ አዳራሽ በውስጥ ይዟል።
በጅማ ከተማ የተገነባው የሀይሌ ሆቴል ከ206 በላይ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ እድል የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ በሙሉ አቅም ሥራ ሲጀምር 400 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ከመፍጠርም ባሻገር ከፍተኛ ጥራት ባለው የአገልግሎት ባህል ህብረተሰቡን ለማገልገል እንዸሚሰራም ተነስቷል።
ለዓለም አሰፋ
ታኀሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
