የዓመት በዓል ገበያው ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ ነው አለ የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ  ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ገሾ፤ከመደበኛው በላቀ ሁኔታ የገና እና ጥምቀት በዓላትን ምክንያት በማድረግ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል።

አቶ ተስፋዬ በክልሉ በሚገኙ 442 የሰንበት ገበያዎች የተለያዩ  የምግብ እህሎች ከ123 ሺህ 473 ኩንታል በላይ ፣አትክልትና ፍራፍሬ ከ 4 መቶ 6 ሺህ በላይ፣የቁም እንስሳትን በተመለከተ ከ500 ሺህ በላይ ይቀርባል ብለዋል።

በተጨማሪም ዘይት ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ፣ዶሮ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ፣እንቁላል ከ30 ሚሊዮን በላይ እና ማር ከ 1 ሺህ 852 ቶን በላይ ይቀርባል ነው ያሉት።

በዓላትን ተከትሎ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪና በህብርተሰቡ ጤና ላይ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዳይኖሩ ግብረሃይል ተቋቁሞ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ሃላፊ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ከመደበኛ ገበያ በበለጠ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረት እንዳይኖር  ሰፊ ስራ መሰራቱን የገለፀው ቢሮ ከአዲስ አበባ ሸማች ማህበራት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የህብረተሰቡን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ ምርቶች በገበያ ላይ እንዳይቀርቡ ክትትል እየተደረገ መሆኑንና ህብረተሰቡ ከመሰል ችግሮች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

በበዓላት ወቅት ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መካከል የሀሰተኛ የብር ኖት ስርጭት አንዱ መሆኑን ያብራሩት ሃላፊው በግብይት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ልኡል ወልዴ

ታኀሣሥ 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *