በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንገድ አለመመቻቸት ለቱሪዝም ዘርፉ እክል ሆኗል ተባለ።

በክልሉ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶች በስፋት የሚገኙ ሲሆን ሆኖም በአንዳንድ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ለመድረስ የመንገድ መሠረተ ልማት ችግር መሆኙን ክልሉ ገልፆል።

አስራ ሁለት ዞኖች ዉስጥ 32 ነባር ብሄረሰቦችን የያዘዉ ክልሉ ባሉት የቱሪዝም ሀብት ተጠቃሚ ለመሆን እየሰራ መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊዉ አቶ ታሪኩ ኦቻ ገልፀዋል።

የመንገድ መሰረተ ልማቱን ለማስፋት በተለይም ከ በጀት ጋር ተያይዞ የሚታዩ እንከኖች ራስን ችሎ ለመስራት ክፍተት እንደፈጠረ አቶ ታሪኩ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በማጎ ብሄራዊ ፓርክ አካባቢ የሚገጥሙ ያለመረጋጋት ሁኔታዎች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጊዜ እንደሚወስድ አንስተዋል።

የመንገድ መሰረተ ልማት ችግሩን ለመቅረፍ በተቻለ አቅም እየተሰራ እንደሆኑ ያነሱት ሀላፊዉ የቱሪዝም ገቢዉ በዚህ አመት ባሉ አምስት ወራት ከፍተኛ ሆኖ መመዝገብን ገልፀዋል።

የቱሪዝም ቢሮዉ ከአጋር አካላት ጋር በመሆኑ የጋሞ የእርቅ ስርአትን÷ ጊፋታ እና የደራሼ የሙዚቃ ስልት የሆነዉን ፊላ በአለምአቀፍ የቅርስ መዝጋቢዉ ድርጅት ዩኔስኮ ለማስመዝገብ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ሰምተናል።

ቁምነገር አየለ

ታኀሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *