” እግዚአብሔር በምድሪቱ ሰላም እንዲያወርድ በመጸለይ፣ እርስ በርስ በመዋደድ፣ በፍቅር እና በእርቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ማክበር እንደሚገባ ” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እግዚአብሔር ሰውን የመውደዱ ዐቢይ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዓለ ልደትን ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ እርቅና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰብ የማስረፅ ሀሳብ ይዘን ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።

የልደተ ክርስቶስ በዓል የእግዚአብሔር በዓል በመሆኑ እግዚአብሔር በምድሪቱ ሰላም እንዲያወርድ በመጸለይ፣ እርስ በርስ በመዋደድ፣ በፍቅር እና በእርቅ ማክበር እንደሚገባ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ለሰው ልጆች ፍቅርንና ሰላምን በመስጠት እንዲሁም በመረዳዳትና በአብሮነት ማክበር እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች ገለፁ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት አባቶች የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በማስመልከት ለመላው የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ታኀሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *