በጋዛ የሟቾች ቁጥር ከተገለጸዉ በላይ 40 በመቶ ከፍ ያለ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

በእስራኤል ሃማስ ጦርነት በጋዛ ህይወታቸዉ አልፏል የተባሉ ሰዎች ቁጥር በ40 በመቶ ዝቅ መደረጉን ነዉ ጥናቱ የጠቆመዉ፡፡

ጦርነቱ በተጀመረበት የመጀመሪያ 9 ወራት ጊዜ ዉስጥ ህይወታቸዉ አልፏል ተብሎ በፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር ይፋ የተደረገዉ ቁጥር በ40 በመቶ ዝቅ የተደረገ ነበር ተብሏል፡፡

እስካለፈዉ ዓመት ሰኔ 30 ድረስ ሚኒስቴሩ ህይወታቸዉ አልፏል ብሎ ይፋ ያደረገዉ የሟቾች ቁጥር 37 ሺህ 8መቶ77 ነበር፤ ጥናቱ የተለያዩ ቁጥሮችን አሰባስቦ አገኘሁት ባለዉ መረጃ ደግሞ በወቅቱ ህይወታቸዉ ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ55 ሺህ እስከ 78 ሺህ ድረስ ይገመታል፡፡

የጥናት ዉጤቱ አጠጋግቶ ያመጣዉ ቁጥር 64ሺህ 2መቶ60 ሲሆን፤ ይህም ሚኒስቴሩ በወቅቱ የሟቾችን ቁጥር በ41 በመቶ ቀንሶ ነበር ማለት ነዉ፡፡

ይህም ቁጥር በጋዛ ከጦርነቱ በፊት ከነበሩ ነዋሪዎች 2.9 በመቶዎቹን የሚወክል ነዉ ፡፡ይህም ማለት ከ35 ነዋሪዎች 1 ሰዉ ህይወቱ አልፏል ፡፡

በእንግሊዝ አጥኚዎች የተመራዉ ይህ ጥናት ፤ ከሟቾቹ መካከል 59 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች፣ ህጻናት እንዲሁም አረጋዊያን ነበሩ ብሏል ሲል ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *