ኢትዮጵያ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት በሰው ሕይዎት እና በንብረት ላይ ባደረሰው ጉዳት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገልፃለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ÷ በደረሰው ጉዳት ኢትዮጵያ ማዘኗን አስታውቋል፡፡
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ከአሜሪካ መንግሥትና እንዲሁም በሎስ አንጀለስ አካባቢ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጎን መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም
