የንብረት ታክስ አዋጁ ደሀውን ማህበረሰብ ይጎዳዋል በሚል ትችት ቀረበበት

የንብረት ታክስ አዋጁ የመንግስት ሰራተኞችን ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንዳይከታቸው ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባም አባላቱ ጠቁመዋል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ጉባዔው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት አቅርቧል፡፡

ከአባላቱ ለምክር ቤቱ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ማህበረሰቦች ምንም እንኳን ንብረት ቢኖራቸውም ገቢያቸው ስለሚያነስ ለተለያዩ ችግሮች ሊጋለጡ ይችላሉ ተብሏል፡፡

የንብረት ታክስ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የንብረት ባለቤቶችን የሚፈትን ነው በሚልም ከምክር ቤቱ አባላት ትችት ቀርቦበታል፡፡

የመንግስት ሰራኞች አንድ ወይ ሁለት ቤት ሊኖራቸው ይችላል ግን በተለያየ መንገድ የሚያገኙት ገቢ ታክስ ስለሚደረግ በሰፊው ለችግር የሚጋለጡበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችልም አባላቱ ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 18 ላይ ታክስ ለመከፈል የማያስችላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ ታክስ ውጪ ናቸው በሚል መቅረቡን የሚያነሱት አባላቱ የመንግስት ሰራተኞችም በዚህ ውስጥ ሊካተቱ ይገባ ነበር ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ውይይቱ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ተፈጻሚነት የሚኖረው የንብረት ታክስ አዋጅን በአራት ተቃውሞ በአስር ድምጸ ተዓቅቦና በአብላጫ ድምፅም አጽድቋል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *