6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ጉባዔው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ያቀረበውን የስንብት ውሳኔ አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *