ምክር ቤቱ በ6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካሉት ሰባት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሳምሶን መኮንን፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተሸሟል፡፡
በመጋቢት 2013 ዓ.ም የወጣው ይኸው አዋጅ፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሰየም ይደነግጋል።
ምክር ቤቱ ዋና ዳይሬከተሩን የሚሰይመው፤ በመንግስት አቅራቢነት እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል። በባለስልጣኑ ቦርድ አማካኝነት የሚሰየመው ዋና ዳይሬክተር፤ “ከማንኛውም ፓርቲ አባልነት ነጻ መሆን” እንደሚኖርበትም በአዋጁ ላይ ሰፍሯል።
ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም
