በስርቆት ያጣውን ከ4 ሚለየን ብር በላይ የኃይል ፍጆታ ሂሳብ ገንዘብ ማስከፈሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ቆጣሪዎችን በመነካካት የኃይል ስርቆት በፈፀሙ የወፍጮ ቤት፣ የዳቦ እና የእንጀራ መጋገሪያ ቤት ደንበኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በተያዘው በጀት አመት 18 ዘመናዊ ቆጣሪዎች ላይ የኃይል ስርቆት መፈጸሙን ገልጹ በስርቆት ያጣውን ከ4 ሚለየን ብር በላይ የኃይል ፍጆታ ሂሳብ ገንዘብ ማስከፈሉን በሪጅኑ የኢነርጂ ማኔጅመንት ኃላፊ አቶ ለሚ አዱኛ ተናግረዋል፡፡

አቶ ለሚ 11 ሥርቆት የፈፀሙ ድርጅቶች ላይ ከ5 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር ቅጣት እንዲቀጡ ማድረጉንና በስርቆት ወቅት ለተበላሹ ቆጣሪዎች 18 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የኃይል ስርቆት መረጃው የተገኘው ተቋሙ በሚጠቀመው መተግበሪያ አማካኝነት ሲሆን በዚህ ዓመት ብቻ በኃይል ሥርቆት ላይ በተሳተፉ ስምንት ደንበኞች ላይ ክስ ተመስርቶ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነና ሦስቱ በሂደት ላይ መሆናቸውን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *