15ኛዉ አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጥናትና ምርምር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጉባዔዉን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ ሲሆን፤ ለሶስት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በጉባዔዉ ላይ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት፤በኢትዮጵያ 5 ሚሊየን መስማት የተሳናቸዉ ዜጎች አሉ፡፡
የምልክት ቋንቋን በማስፋት መስማት የተሳናቸዉ ዜጎች የሚገጥማቸዉን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚያስችል አሰራር መዘርጋት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በአገራችን ካሉ መስማት የተሳናቸዉ ዜጎች ቁጥር አንጻር ፤ይህ የምልክት ቋንቋ ጥናትና ምርምር መካሄዱ ትልቅ ፋይዳ እንዳለዉም ነዉ ሚኒስትሯ የገለጹት፡፡
ጉባኤዉ መዘጋጀቱ መስማት የተሳናቸዉ ዜጎችን እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ እና የምልክት ቋንቋን በማስፋት ያሉትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለዉም ተገልጿል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም
