በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ  የ 21ኛ ሳምንት መርሐግብር

ማንችስተር ሲቲ ፣ ቼልሲ እና ሊቨርፑል  ነጥብ ጣሉ!

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር  ያደረገውን ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የኖቲንግሀምን ግብ ክሪስ ውድ ሲያስቆጥር ዲያጎ ጆታ ሊቨርፑልን አቻ አድርጓል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የማንችስተር ሲቲን  ሁለት  ግቦች ፊል ፎደን  ሲያስቆጥር ለብሬንትፎርድ ዊሳ እና ኖርጋርድ ከመረብ አሳርፏል።

ቼልሲ ከበርንማውዝ ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የሰማያዊዎቹን ግብ ኮል ፓልመር እና ሬስ ጄምስ ሲያስቆጥሩ ክላይቨርት እና ሴሜኒኖ ለበርንማዝ ከመረብ አሳርፈዋል።

የሊግ ደረጃቸው

1 ሊቨርፑል :- 47 ነጥብ
2  ኖቲንግሀም ፎረስት :- 41 ነጥብ
3 አርሰናል :- 40 ነጥብ
4 ቼልሲ :- 37 ነጥብ
5 ኒውካስትል :- 35ነጥብ
6 ማንችስተር ሲቲ :- 35 ነጥብ

ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ ሊጉ ሲቅጥል፣ አርሰናል ከ ቶተንሀም ምሸት  5፡00 ላይ ይፋልማሉ፡፡

ጋዲሳ መገርሳ

ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *