የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተቋሙን ማደራጀት ከጀመረበት 2 ዓመታት ወዲህ ከ57 ሺህ በላይ ዜጎች መሸኛ ማስገባታቸውን ገልጿል።
57 ሺህ 2መቶ14 የሚሆኑ መሸኛዎች መግባታቸውን እና ከዚህ መሐል 25ሺህ 5መቶ81 የሚሆኑት ብቻ ወደ መጡበት ክልል መረጃቸው ተልኮ ማጣራት መደረጉን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ገልጸዋል።
የመረጃውን ጉድለት እና ትክክለኝነቱን ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ወደ መዲናዋ ሀሰተኛ መሸኛዎች ይመጣሉ ነው ያሉት።
መሸኛ ካመጡ መካከል የመረጃቸውን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ 9ሺህ 5መቶ4 የሚሆኑት ለኤጀንሲው ቀርበው ሪፖርት ማድረጋቸውን ዳይሬክተሩ አንስተዋል።
የማስረጃው ትክክለኛነት፣ ፎርጂድ መሆኑ ፣ የማንነት ለውጥ መኖሩን እንዲሁም መሸኛው የተላከለት ግለሰብ የዛ ክልል ነዋሪ ነው ወይ የሚለው ወደ ክልሎች መረጃዎችን ለማጥራት ከሚላኩ ጉዳዮች መካከል ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል።
ወደ መዲናዋ ከሚገቡ ሰዎች መካከል አንድ ሶስተኛውን አግደን ነበር ያሉት ዳይሬክተሩ ፤ አሁንም የመሸኛ ማጥራት እያደረግን ነው ዜጎችን የምንቀበለው ብለዋል።
ይህ የተገለፀው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የ6 ወር አፈፃፀሙን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።
እስከዳር ግርማ
ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም
