በኢትዮ  ጅቡቲ  ኮሪደር  ያለውን  የንግድና የሎጅስቲክስ ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚያስችል ኮንፈረንስ  ማካሄድ ጀመረ፡፡

የኢትዮ ሎጅስቲክስ ዘርፍ ማኅበራት  በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲና በአካባቢው የንግድና የሎጂስቲክስ ኮሪደር ስር ያሉ ችግሮችን ለመቀየር የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር  ማድረግ ጀምሯል።

የኢትዮ ሎጅስቲክስ ዘርፍ ማኅበራት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ጌታሁን የዚህ ምክክር ዋነኛ አላማው  የኢትዮጵያና ጅቡቲን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር እና ለሁለቱም አገራት ዘላቂ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረከቱ እድሎችን ማመቻቸት ነው ብለዋል።

ይህ ኮንፈረንስ አዳዲስ የንግድ ዕድሎችን ለመከፈት፣ በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ እንደሆነ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ገልጸዋል።

የኢትዮ ጅቡቲ ኮሪደር ለኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ኢኮኖሚ ትስስር ወሳኝ መስመር ከመሆን ባለፈ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በማስተዋወቅና በመፍጠር ረገድም ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ጥር  13 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *