የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ሳምንት በአዲስአበባ  መካሄደ ጀመረ

ዝግጅቱ ዲያስፖራዉ በሀገሪቱ የልማት እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያለዉን ተሳትፎ ለማጠናከር ያለመ ነው ቸብሏል።

ዲያስፖራው ለሀገሩ ልማት እና መሰል ስራዎችን ከመስራት አንፃር የላቀ ሚና እንዳለዉ ተነስቷል ፡፡

በዝግጅቱ ላይ ዲያስፖራዎች ወደ ሃገራቸዉ ገብተዉ በልማት ስራዎች፣  በኢንቨስትመንትና በተለያዩ በቱሪስት መዳራሻዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል ፡፡

በተጨማሪም ወደ ሃገር ዉስጥ ገብተዉ በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ዲያስፖራዎች ልምዳቸዉን እንዲያካፍሉ ተጠይቋል ፡፡

ዲያስፖራዎች በበኩላቸው የተለያዩ የልማት አማራጮችን በመመልከት ኢትዮጵያ ገብተዉ ሃገራቸዉን በጋራ ለማሳደግ ያላቸዉን ቁርጠኝነት ገልፀዋል ፡፡

በፕሮግራሙ የተዘጋጀዉ በ ኢግዚቢሺን ማዕከል ነው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ
የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ምርትና  እና አገልግሎታቸዉን ለዲያስፖራዉ የሚያስተዋዉቁበት እንደሆነ  ተነገሯል።

አቤል እስጢፋኖስ

ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *