“ሰላም በሌለበት ምክክር መካሄድ አይችልም የሚል ሃሳብ ከተነሳ አስቻይ ሁኔታ ከፓርቲዎችም ይሁን ከህዝቡ ሊፈጠር ይገባል ነገር ግን ግጭትም እያለ ምክክር መካሄድ ይችላል” የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ ፡፡
በብሔራዊ መግባባት ላይ ያተኮረው ሁለተኛው የፓርላማ የዜጎች መድረክ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ሃሳባቸው ያነሱት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር ) “ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ተከታታይ የፖለቲካ ቀውስ እና አለመግባባት ምን አይነት ሀገራዊ ምክክር ሊደረግ ይችላል ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የሰላም እና የጸጥታ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ቢሆንም የውይይቱ ዋነኛ መወያያ ርዕስ አለመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ለምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ምላሻቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፤ “ሰላም ሳይኖር ምክክር ማካሄድ ከባድ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በግጭት ውስጥም ምክክር ማካሄድ እንሚቻል የብዙ ሃገሮችን ተሞክሮ መወሰድ ይገባል” ብለዋል፡፡
አስቻይ የምክከር መድረክ መፈጠር ዋነኛ መፍትሔ ነው የሚሉት አቶ መስፍን ለዚህም ፓርቲዎችም የሃገር ሽማግሌዎችም ይህንን ልትወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን እንደ ሃገር መከላከያ ሁሉ ኮሚሽኑም የማንም ወገንተኝነት የለበትም አዋጁም አይፈቅድም ብለዋል ፡፡
ኮሚሽኑ ተወካይነቱ ለህዝብ በሃገሪቱ ላሉ ሁሉም ፓርቲዎች እንዲሁም ለፌድሬሽን ምክረ ቤቶች ጭምር እንጂ በግል የሚወክለው እንደሌለ ህዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል፡፡
ለአለም አሰፋ
ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም
