የበለስ ስኳር ፋብሪካ በሃይል እና በገንዘብ እጥረት ስራ አቁሟል ተባለ

የበለስ ስኳር ፋብሪካ በሃይል እና በገንዘብ እጥረት ስራ አቁሟል ተባለ

ፋብሪካው ስራ በማቆሙ ምክንያት ለሰራተኛው የ4 ወር ደሞዝ መክፈል አልቻለም ተብሏል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ሲሆን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያደመጠ ይገኛል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስተር አቶ መላኩ አለበል፤ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል፡፡

አባለቱም ለሚኒስትሩ የመንግስት ፋብሪካዎች ችግር ላይ ናቸው በደንብ ሊፈተሹ ይገባል ብልዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ ለአብነት የመንግስት ስኳር ፋብሪካዎችን ያነሱ ሲሆን፤ ፋብሪካዎቹ አሁን ላይ ችግር ውስጥ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የበለስ ስኳር ፋብሪካ በምሳሌነት የቀቧል ፤ የበለስ ስኳር ፋብሪካ በአመት 242 ቶን ማምረት የሚችል ቢሆንም በሃይል አቅርቦት እና በገንዘብ እጥረት ምክንያት ስራ አቁሟል ፡፡

ፋብሪካው በዚህም ሳቢያ የ4 ወር ደሞዝም ለሰራተኞች መከፈል አለመቻሉ ተነስቶ ምክንያቱ ደግም የሃይል እና የገነዝብ አቅርቦት እጥረት ነው ይሄ ችግር ቀደም ብሎ ሊፈታ ይገባ ነበር ብለዋል፡፡

አባላቱ አምራች ኢንዱስትሪውን በግብዓትም ይሁን በሃይል አቅርቦት ሊደገፍ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የበለስ ስኳር ፋብሪካ በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳ የሚገኘ ሲሆን በ2014 ዓ.ም የስኳር ማምረት ስራውን መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የሚኒስቴሩን የ2017 ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ሲያቀርቡ በግማሽ ዓመቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች 369 ሚሊየን 110 ሺህ ዶላር የውጭ ምንዛሪ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡

በሪፖርታቸውም÷በግማሽ ዓመቱ ለተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን በላይ ግብዓት ማቅረብ ተችሏል ብለዋል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *