በኦሮሚያ ክልል በህገወጥ የንግድ ስራ ላይ በተገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ በተጣለ ቅጣት ከ24 ሚሊዩን ብር በላይ ተሰብስቧል ተባለ።

በበጀት አመቱ አጋማሽ በክልሉ ህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የንግድ ድርጅቶች 24 ሚሊየን 745 ሺህ 142 ብር ከቅጣት መሰብሰቡን የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ገልፆል።

የቢሮዉ የኢንስፔክሽና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸዉ ቆጲሳ፤ በባለፉት 6 ወራት 6 መቶ 21 ሺህ ተቋማት ላይ ቁጥጥር ማድረጋቸዉን ለኢትዩ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በዚህም 92 ሺህ 621 ነጋዴዎች ያለንግድ ፍቃድ ሲነግዱ፣ከዘርፍ ውጪ ሲነግዱ፣ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅሎ በመሸጥ፣ንግድ ፍቃድ ሳያድሱ፣ዋጋ ሳይለጥፉ፣ዋጋ ጨምሮ በመሸጥ ላይ ተሰማርተው ነበር ብለዋል።

በእነዚህ በህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ ህጋዊ እርምጃ ከ 24 ሚሊየን ብር በላይ በቅጣት መገኘቱን የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ የኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ቆጲሳ ጫካ ተናግረዋል።

በእርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል 32 ሺህ 350 የታሸጉ ሲሆን 382 የሚሆኑት የንግድ ፍቃዳቸው መሰረዙን ሰምተናል።

ከዚህ በተጨማሪም በተቋማቱ ላይ የእገዳ እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉ ገልፀዋል ።

ዳይሬክተሩ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በነዚህ ተቋማት ላይ በተደረገ የቁጥጥር ስራ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

ልኡል ወልዴ

ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *