2ሺህ ፍልስጤማዊያን ቤተሰቦች በእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት ምክንያት ከጄኒን መጠለያ ጣቢያ መፈናቀላቸዉ ተገለጸ፡፡

ሶስተኛ ቀኑን በያዘዉ የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት በጄኒን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ 2 ሺህ ቤተሰቦች መፈናቀላቸዉ ተገልጿል፡፡

የእስራኤል ጦር ነዋሪዎች ከመሸ እንዳይወጡ ከልክሎ ሐሙስ ጠዋት እንደገና እንዲሞክሩ ከማሳወቁ በፊት ብዙ ቁጥር ያለዉ ህዝብ መፈናቀሉን የአከባቢዉ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

በጄኒን ከተማ ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዳይንቀሳቀሱ ገደብ የተጣለባቸዉ በመሆኑ፤በመንደሮች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች የተፈናቃዮችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

የተፈናቀሉ ሰዎች ያሉበት ሰብዓዊ ሁኔታ “አስጨናቂ” ነው ሲሉ የአከባቢዉ ባለስልጣናት ሁኔታዉን ገልጸዉታል፡፡

የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ለአናዶሉ የዜና ወኪል እንደገለጹት፤ የእስራኤል ጦር በካምፖቹ ዉስጥ ያሉ ተፈናቃዮች፤ ህመምተኞች እና በዕድሜ የገፉትን ጨምሮ ከስፍራዉ በእግራቸዉ እንዲሸሹ አድርጓል ብለዋል፡፡

ጦሩ ባደረሰዉ ጥቃትም 10 ፍልስጤማዊያን ሲገደሉ፤ 40 የሚሆኑት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

እንደ ፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ፤ በዌስት ባንክ የእስራኤል ጦር ባደረሰዉ ጥቃት እስካሁን 8መቶ70 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ፤ 6ሺህ 7መቶ የሚሆኑት ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *