የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገሪቱ በአዉሮፓ ካሏት ወታደሮች ዉስጥ 20ሺህ የሚሆኑትን እንደቀሚቀንሱ ተነግሯል፡፡
ይህም አሜሪካ በአዉሮፓ ያሰፈራቻቸዉን 1 መቶ ሺህ ወታደሮች ወደ 80 ሺህ ዝቅ የሚያደርግ ነዉ፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን የአሜሪካ ወታደሮች በአዉሮፓ እንዲቆዩ ከተፈለገ አህጉሪቱ ክፍያ እንድትከፍላቸዉ የትራምፕ አስተዳደር ይፈልጋል ሲል የጣሊኑ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
ምክንያቱም በአሜሪካ በጀት ብቻ የአዉሮፓ ምድር ልትጠበቅ አይችልም ብለዋል፡፡
አዉሮፓና አሜሪካ ለዩክሬን የሚያደርጉት ድጋፍም እኩል መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
አሜሪካ ለሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ የምታወጣዉን በጀት እንደምትቀንስ ትራምፕ መናገራቸዉ የሚ ታወስ ነዉ፡፡
ይህንንም ተከትሎ ፈረንሳይና ጀርመን የትራምፕን አስተዳደር ለአዉሮፓ አ ህልዉና አደጋ ነዉ ሲሉ እየወቀሱ ነወ ፡፡
አባቱ መረቀ
ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም
