የናይጄሪያ መከላከያ ሚኒስትር በሰሜናዊ ምስራቅ ቦርኖ ግዛት ባካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች መግደሉን ገልፆል።
በዚህ ዘመቻም 70 የቡድኑ ታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን ከተገደሉት ታጣቂዎች ዉስጥም የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙበት መከላከያ ሚኒስትሩ ያወጣዉ መግለጫ አመላክቷል።
በፈረንጆች 2000 አመት ጀምሮ በናይጄሪያ ይህ አማፂ ቡድን በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት የተቀጠፈበትን የጅምላ የሽብር ጥቃት ፈፅሟል።
አሁንም እየቀጠለ ባለዉ የአማፂያኑ ጥቃት ምክንያት 100ሺህ በላይ ናይጄሪያዉያን ቤታቸዉን ጥለዉ እየተሰደዱ ይገኛሉ ተብሏል።
ከጥር 16-25 በናይጄሪያ የመከላከያ ጦር ተደርጓል በተባለዉ ዘመቻ አማፂያኑ ከመግደል ባለፈ በዘመቻዉ የናይጄሪያ ወታደሮች መቁሰላቸዉን የጦሩ መግለጫ አያይዞ ጠቅሷል።
አሸባሪዉ ቦኮ ሃራም የሽብር ጥቃቱን ከናይጄሪያ በተጨማሪ ወደ ካሜሮን÷ ቻድ÷ ኒጀር እየፈፀመ ይገኛል ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ ነው።
ቁምነገር አየለ
ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም
