የቢላልን አዛን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ  እየተሰራ መሆኑን  የዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርዓን ማህበር አስታወቀ ፡፡

በኢስላም ታሪክ የመጀመርያውን የሶላት ጥሪ ያሰማነው ነዉ ተብሎ የሚታሰበዉ የቢላል-አል-ሀበሺ አዛን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ  እየተሰራ መሆኑን የዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርዓን ማህበር አስታዉቋል

የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ኡስታዝ ኑረዲን ቃሲም ለጣቢያችን እንደገለፁት በታሪክ  የሰላት ጥሪ አድራጊ ኢትዬጵያዊ ቢላል ቢሆንም  ሌሎች ሀገራትም የእኛ ነው እያሉ የባለቤትነት ክርክር ያስነሱ  መኖራቸውም ተናግረዋል ፡፡

ቢላል-አል-ሀበሺ  ኢትዮጵያዊ መሆኑን አረጋግጦ  በዩኒስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ አዲስአበባ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል ፡፡

ሁለተኛው ዙር 2025  አለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ወድድር በኢትዮጵያ መካሄዱ ደግሞ ለማስመዝገብ እየተሰራ ላለዉ ስራ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስቴር የቢላልን አዛን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተሰምቷል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *