የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ተጨዋች ሌዊስ ስኬሊ በዎልቭስ ጨዋታ የተመለከተው ቀይ ካርድ እንደተነሳለት ይፋ ተደርጓል።
አርስናል ተጨዋቻቹ የተመለከተው ቀይ ካርድ ተገቢ አይደለም በሚል ይግባኝ ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል።
የእንግሊዝ ኤፍኤ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ሌዊስ ስኬሊ የተመለከተው ቀጥታ ቀይ ካርድ መሰረዙን አስታውቋል።
ይህንንም ተከትሎ ሌዊስ ስኬሊ አርሰናል የፊታችን ዕሁድ ከማንችስተር ሲቲ በሚያደርገው ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ የሚደርስ ይሆናል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም
