ከሦስት መቶ ሺህ በላይ ፍልስጥኤማዊያን ወደ ቀያቸው መመለሳቸው ተዘግቧል

በጋዛ የተቀሰቀሰውን ጦርነት በመፍራት የተፈናቀሉ ከሦስት መቶ 70 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ወደ ሰሜናዊ ጋዛ መመለሳቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ሰርጥ መንግሥት ባለስልጣናት ተናገሩ።

ተፈናቃዮቹ የተመለሱት እስራኤል የፍተሻ ኬላዎቹን ከፍታ እንዲመለሱ መፍቀዷን ተከትሎ ነው።

ፍልስጥኤማዊያኑ አብዛኞቹ በእግራቸው ረጅም ርቀት በመጓዝ ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው ተብሏል፡፡

እስራኤል የሐማስ ታጣቂዎችን እና ፈንጂ ያጠመዱባቸውን ህንጻዎች ዒላማ አድርጋ ባደረሰችው የቦምብ ድብደባ አብዛኛው አካባቢ ወድሟል።

እስራኤል እ አ አ በ2023 ጥቅምት ውስጥ ጥቃቱን እንደጀመረች ወደአንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ እንዲወጡ ማዘዟ የሚታወስ ነው፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ እስካሁን ሰባት ታጋቾች ከጋዛ ሲለቀቁ እስራኤል ሦስት መቶ የሚሆኑ ፍልስጥኤማዊያን እሥረኞች ለቃለች ። ሰብዓዊ ረድዔትም በብዛት ወደጋዛ መግባት ጀምሯል ብሏል አልጀዚራ በዘገባው ።

ሐማስ በመጀመሪያው የተኩሥ አቁም ምዕራፍ ሐማስ ተጨማሪ ታጋቾችን በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ እንደሚለቅም ይጠበቃል፡፡እስራኤል ከሀማስ አረጋግጫለው እንዳለችው ስምንት የሚሆኑ ታጋቾች ህይወታቸው አልፏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከጥቅምት 2023 ጀምሮ 70 በመቶው የጋዛ ሰርጥ ህንጻዎች ተበላሽተዋል ወይም ወድመዋል፣ በተለይ ደግሞ በሰሜናዊ ግዛት ያለው አብዛኛው ህንጻዎች የከፋ ውድመት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡

በጋዛ የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ (ኡንዋ) ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሳም ሮዝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሰሜናዊ ጋዛ ያለው ህዝብ “በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።

ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *