ሉክ ሾው  ወደ ልምምድ ተመልሷል !

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው የቡድን ልምምድ መጀመሩ ተነግሯል።

በተጨማሪ ማርከስ ራሽፎርድ ፣ አሌሀንድሮ ጋርናቾ እና ካሴሚሮ ከቡድኑ ጋር ልምምዳቸውን መስራታቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ነገ ምሽት የዩሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታውን  5:00 ከ ሮማኔያው ከለብ  FCSB የሚያደርግ ይሆናል።

አሁን  ላይ  በማንችስተር ዩናይትድ  ቡድን  ጉዳት ላይ ያሉ ተጨዋቾች ሜሰን ማውንት እና ጆኒ ኢቫንስ ብቻ ናቸው።

የተቀሩት ሁሉም  የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ዛሬ በተደረገው የቡድኑ ልምምድ ላይ ተሳትፈዋል።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *