የመንገደኞች አውሮፕላኑ ገጭት ያጋጠመው በስልጠና ላይ በነበረ የጦር ሂሊኮፕተር ጋር ነበር ተብሏል፡፡
በአደጋው እስካሁን የ18 ሰዎች አስክሬን መገኘቱ ተነግሯል፡፡
ንብረትነቱ የአሜሪካ አየር መንገድ የሆነው የመንገደኞች አውሮፕላን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሮናልድ ሬገን ብሄራዊ አየር ማረፊያ ሲቃረብ ከጦር ከሄሊኮፕተሩ ጋር መጋጨቱን የሀገሪቱ ባለስልጠናት ተናግረዋል።
አውሮፕላኑ 60 መንገደኞች እና አራት የበረራ ሠራተኞች ጭኖ እንደነበር የታወቀ ሲሆን ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሶስት የአሜሪካ ወታደሮችን ጭኖ እንደነበር ተነግሯል።
አደጋ የደረሰበት ይህ መለስተኛ አውሮፕላንም ዲሲ በሚገኘው ፖቶማክ የተሰኘ ወንዝ ላይ ሳይወድቅ እንዳልቀረ ተነግሯል፡፡
የነፍስ አድን ሰራተኞች እና ጀልባዎች ወደ አካባቢው ተሰማርተዋል ተብሏል።
የሀገሪቱ የአቪዬሽን አስተዳደር እንዳስታወቀው፤ አውሮፕላኑ የአሜሪካ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 5342 የሆነ እና ከዊቺታ ካንሳስ የተነሳ መሆኑን ገልጿል።
የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር በአደጋው ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሬገን ብሄራዊ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በተሳፋሪ ጄት እና በጦር ኃይሎች ሄሊኮፕተር መካከል የደረሰውን የአውሮፕላን ግጭት ተከትሎ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር ሲሉ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የውሰው ገዝሙ
ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም
