በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ በክልሉ 53 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ብቻ በጤና ተቋም ወልደዋል፡፡

በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልሰው ጫንያለው እንደተናገሩት በክልሉ በ6 ወር አፈጻፀም 53 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ብቻ ናቸው በጤና ተቋም መውለድ የቻሉት ብለዋል።

አቶ መልሰው 47 በመቶው የሚሆኑ እናቶች ግን በክልሉ በተፈጠረው የፀጥት መደፈረስ ምክንያት ወደ ጤና ተቋም መጥተው መውለድ እንዳልቻሉ ነግረውናል።

በክልሉ ባለፋት ጊዜያት የትራንስፖርት የመቋረጥ እና የግብአት ችግር እናቶች በተቻለ መልኩ የወሊድ ጊዜያቸውን መከታተል እንዳልቻሉም ነግረውናል።

ዳይሬክተሩ፤ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ዜሮ ሪፖርት ያስመዘገቡ አሉ ያሉ ሲሆን ለአብነትም የምስራቅ ጎጃም እና የሰሜን ወሎ ዞኖችን ጠቅሰዋል።

ከቅርብ ጊዜ በኋላ ግን ነገሮች እየተስተካከሉ መምጣታቸውን በማንሳት ከአጋር አካላት ጋርም በጋራ እየሰሩ እንደሆነም ነግረውናል።

በሌላ በኩል በክልሉ ባለው የጸጥታ እና የእንቅስቃሴ ችግር ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ዩኒት ደም መሰብሰብ እየቻሉ አለመሆናቸውንም ዳይሬክተሩ ጨምረው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ለአለም አሰፋ

ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *