በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎችን በማስቀረት የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ በመሆኑ ዘርፉ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።
አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና የንግድ ተቋማት የፈርኒቸር ዘርፉን ደጋፊ መሆናቸውም ተገልጿል።
የተለያዩ ጥናቶች በምስራቅ አፍሪካ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት የፈርኒቸር፣ የቤተ-ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ኢንዱስትሪ ምርቶች እና አገልግሎቶች የገበያ ፍላጎት በእጥፍ እንደሚጨምር ያሳያሉ ነው የተባለው።
የመሠረተ ልማት እና ሌሎች ግንባታዎች የገበያው ፍላጎት እንዲያድግ በማድረጋቸው ለፈርኒቸር ፣ ቤተ-ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ዘርፎች የፈጠራ ስራቸው እንዲጨምር መንገድ መክፈታቸው ተገልጿል።
አገራችን የፈርኒቸር ፣ ቤተ-ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ኢንዱስትሪ ዘርፍን ለመደገፍ እና ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ለማረጋገጥ የተለያዩ ዝግጅቶችን ማከናወን አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።
በዚህም መሰረት 5ተኛው ፊንቴክስ የቤተ-ውበትና የግንባታ አጨራረስ አውደ-ርዕይ ተከፍቷል።
በአውደ-ርዕዩ ላይ ከ4ሺህ በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የንግዱ ማህበረሰብ የንግድ ትስስር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሚቀጥሉት አመታት በሚኖሩ ዝግጅቶች ላይ የውጭ አገር ተቋማትም ሊሳተፉ የሚችሉበት ዕድል መኖሩ የተገለፀ ሲሆን፤በዚህኛው ዙር 40 የአገር ውስጥ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉም አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
ከጥር 22-25 2017 በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደው ይህ ዝግጅት “ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ተገልጿል።
አውደ-ርዕዩን ፕራና ኤቨንትስ እና አፍሪካን ትረስትድ ፓርትነርስ በጋራ አዘጋጅተውታል።
እስከዳር ግርማ
ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም
