ሐማስ በዛሬው እለት ስምንት ታጋቾችን ለቋል

እስራኤልና ሐማስ በደረሱት ስምምነት መሰረት ዛሬም የታገቱ እስራኤላውያን ለአለም አቀፊ ቀይ መስቀል አስረክቧል፡፡

ሐማስ በጣሬው ዕለት አንዲት እስራኤላዊት ወታደር ጨምሩ 8 ታጋጆች ለቀይ መስቀል አስረክቧል።

ሐማስ በተለይ በቁጥጥሩ ሥር የነበረችውን እስራኤላዊት ወታደር ለቀይ መስቀል ያስረከበው በሰሜን ጋዛ በጃባሊያ አካባቢ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ከሰጠው መግለጫ ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል አምስት የታይላንድ ዜጎችም ይገኞበታል ።

ሰባቱ ታጋቾች አሁን ወደ እስራኤል ግዛት መሻገራቸውን እስራኤል ትናገራለች።

የእስራኤል የመከላከያ ሃይል እንዳለው “የተመለሱት ታጋቾች ወደ ደቡብ እስራኤል የመጀመሪያ መቀበያ ቦታ እየሄዱ ነው።”

ከሰባቱ ታጋቾች ሁለት እስራኤላውያን ( ወንድና አንዲት ሴት) እና አምስት የታይላንድ ዜጎች ይገኙበታል። የአይዲኤፍ መግለጫ እንደገለጸው አምስቱ ታይላዳዊያን ከታይላንድ መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚገናኙ ተናግሯል።

ስምንተኛው ታጋች አጋም በርገር ቀደም ብሉ መለቀቁ እና ወደ እስራኤል መሻገሩ ቢቢሲ ጨምሩ ዘግቧል፡፡

ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *