ማንችስተር ዩናይትድ ከሮማንያው ክለብ ስቱዋ ቡካሬስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የቀያዮቹ ሴጣኖችን የማሸነፊያ ግቦች ዲያጎ ዳሎት እና ኮቢ ማይኖ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ቶተንሀም ከኤልፍስቦርግ ጋር ያደረጉትን የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ 3ለ0 አሸንፈዋል።
ቶተንሀም የማሸነፊያ ግቦች ስካርሌት ፣ አጃይ እና ሚኪ ሞርከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች አሸንፈዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ አሁን በኢሮፓ ሊጉ ብቸኛዉ ያልተሸነፈዉ ቡድን ነዉ ፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ላዚዮ ፣ አትሌቲክ ቢልባኦ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ቶተንሀም ፣ ፍራንክፈርት ፣ ሊዮን ፣ ኦሎምፒያኮስ እና ሬንጀረስ 16ቱን ተቀላቅለዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም
