85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል በእንጅባራ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል “አርበኝነታችን ለአኹናዊ ሰላማችን”በሚል መሪ መልዕክት በደመቀ ኹኔታ በእንጅባራ ከተማ በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ ፈረሶችና ፈረሰኞች ለሀገር ነጻነት ሲሉ የከፈሉትን መስዋዕትነት እና የከፈሉትን ዋጋ በማሰብ የሚከበር በዓል ነውም ተብሏል።

በዓሉ ሲከበርም አባት አርበኞች የጣሊያን ወረራን በፈረሶቻቸው ታግዘው የቀለበሱበት፣ ያመጡትን ድል እና ነጻነት የሚታወስበት ነው መሆኑም ተነግሯል ።

የአገው ፈረሰኞች ማኅበር አለቃ ጥላየ አየነው 85ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበርን በየዓመቱ ስናከብር ነጻነታችን ብዙ ዋጋ ተከፍሎበት የመጣ መኾኑን እያሰብን ነው መሆን ያለበት ብለዋል።

ከሁሉም በላይ ግን ፈረስ ለአገው ሕዝብ ሁለ ነገሩ እንደኾነ ገልጸዋል።

ፈረስ ለአገው ሕዝብ የልማት ማሳለጫ ሀብቱ፣ በደስታ ጊዜ መድመቂያው፣ በሀዘን ጊዜ ደግሞ ማልቀሻው እንደኾነ ተናግረዋል።

የአገው የፈረሰኞች ማኅበሩ በየዓመቱ እየደመቀ እና እየጎለበተ መምጣቱንም አቶ ጥላየ አየነው ተናግረዋል።

ማኅበሩ ከ6ሺህ 4መቶ በላይ ኮሚቴዎች በአሁን ሰዓት እንዳሉትም በክብረ በዓሉ መክፈቻ ንግግር ላይ  አቶ ጥላየ አየነው ገልጸዋል።

ልኡል ወልዴ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *