መድፈኞቹ ሲቲ ላይ ጣፋጭ ድል ሲቀዳጁ ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ካይ ሀቨርትዝ ፣ ንዋኔሪ ፣ ሌዊስ ስኬሊ እና ቶማስ ፓርቴ ማስቆጠር ችለዋል።

አርሰናል ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ሲቲ ላይ ከአራት በላይ ግቦችን አስቆጥሮ ማሸነፍ ችሏል።

አርሰናል ማንችስተር ሲቲን በኤምሬትስ በተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ከአስራ ስድስት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ማንችስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የክሪስታል ፓላስን የማሸነፊያ ግብ ማቴታ ሁለቱንም ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ አስራ አንደኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የክሪስታል ፓላሱ የፊት መስመር ተጨዋች ማቴታ በውድድር ዘመኑ አስረኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

በሌላ ጨዋታ ቶተንሀም ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ሳር እና ጃኔልት በራሱ ላይ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2ለ0 አሸንፈዋል።

ቶተንሀም ከአራት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ሶስት ነጥባቸውን አሳክተዋል።

ዛሬም ሊጉ ሲቀጥል፡-ምሽት 05:00 ላይ ስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ከ ዌስትሃም ይፋለማሉ ።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *