የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር በግዛታችን እንዳይዘመር ሲሉ ካናዳዊያን ተቃወሙ።

የበረዶ ኳስ ጨዋታ (ሆኪ) መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ካናዳዊያን የአሜሪካን ብሔራዊ መዝሙር እንዳይዘመር ሲሉ ተቃውሟል።

ካናዳዊያኑ ደጋፊዎች ይህን ያደረጉት የዶናልድ ትራምፕን የታሪፍ ጭማሪ በመቃወም ነው።

በካናዳ ዋና ከተማ ኦቶዋ እየተካሄደ በነበረው የብሔራዊ ሆኪ ሊግ የአሜሪካ ቡድን ተጋጣሚ ሆኖ የቀረበሲሆን በዚህ ወቅት ነው ብሔራዊ መዝሙር እንዳይዘመረ የተቃወሙት።

ጥብቅ ወዳጅ በሆኑት ካናዳዊያንና አሜሪካዊያን ዘንድ እንዲህ ያለ ተግባር የሚታሰብ አልነበረም ተብሏል ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ ምርቶች ላይ የ25 በሐቶ ጭማሪ ማድረጋቸው የንግድ ጦርነት እንዳይፈጥር ተሰግቷል።

ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ከካናዳ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ማናቸውም ሸቀጦች የ25 % ታሪፍ የሚታከልባቸው ሲሆን በነዳጅ ላይ ደግሞ የ10% ታሪፍ ይደመራል።

ይህ የካናዳን ወጪ ንግድ ክፉኛ ይጎዳዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ልኡል ወልዴ

ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *