ለወንጀል መንስኤ የሆኑ አዋኪ ድርጊቶችን ለማስወገድ የሚያከናውነውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ፤ በተለያዩ አካባቢዎች ህጋዊ የንግድ ሽፋንን ለህገ ወጥ ተግባር በማዋል ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም አዋኪ ድርጊት ሲፈፀምባቸው የተገኙ የተለያዩ ሆቴሎች፣ ቪላ ቤቶች፣ የሌሊት ጭፈራ ቤቶች እና ሌሎች የንግድ ተቋማት ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም፣ ህገ ወጥ ተግባሩን ሲፈፅሙ እና ሲያስፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦችም በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆኑ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ሰሞኑንም የወንጀል መንስኤ እና የህብረተሰቡ የፀጥታ ስጋት የሆኑ አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ቤቶች ውስጥ የተገኙ ግለሰቦች በሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሷል፡፡

በተለይም በቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ቤቶች ውስጥ የተገኙ ግለሰቦች በጊዜያዊነት ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ተደርጎ ለፈፀሙት የደንብ መተላለፍ ጥፋት ጉዳዩ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንቡ መሰረት የገንዘብ ቅጣት እንዲጣልባቸው መደረጉን የአዲስ አበባ ፓሊስ ያደረሰን መረጃ ያመላክታል

ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *