አዋሽ ባንክ 2ተኛዉን ምዕራፍ የ”ቀጠሌወን” የስራ ፈጠራ ዉድድር የማጠቃለያ መርሃግብርም አካሂዷል፡፡
መርሃ ግብሩ ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑንም ባንኩ አስታዉቋል፡፡
በማጠቃለያ መርሃግብሩ ላይ በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ተሽከርካሪ የሰራ ወጣት ያሸነፈ ሲሆን፤ የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጠዉ እና አምስት ሚሊየን ደግሞ በብድር መልክ እንደሚያገኝ ተገልጿል፡፡
ሌሎች አምስት ተወዳዳሪዎች ከ200 ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር በሽልማት መልኩ ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዚህ ውድድር ከ6ኛ እስከ 8ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎችም የገንዘብ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፤ከ80 ሺህ እስከ 1መቶሺህ ብር ሽልማት አግኝተዋል ፡፡
በሁለተኛው ምዕራፍ የ‹‹ቀጠሌወን›› ውድድር ተወዳዳሪዎች መሰረታዊ የቢዝነስ ንድፈ-ሀሳብ አዘገጃጀት፣ ቢዝነስ ፕላን አቀራረፅ፣ የተግባቦት እና ክህሎት የመሳሰሉ መሰረታዊ ዕውቀቶችን ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉንም ባንኩ አስታዉቋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም
