የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ጦራቸዉ ጋዛ የሚኖሩ ፍልስጥኤማዉያን ግዛቲቱን «በፈቃደኝነት»እንዲለቁ የሚያችል» ዕቅድ እንዲነድፍ ማዘዙ ተሰማ፡፡

የሚንስትሩ ትዕዛዝ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥን ለመቆጣጠር እንደሚፈልጉ ካስታወቁ በኋላ ዓለማቀፍ ተቃዉሞ እየተሰማ ባለበት ወቅት ነው።

የመከላከያ ሚንስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ ትራምፕ ከ2 ሚሊዮን በላይ ፍልስጥኤማዉያን የሚኖሩባትን ጋዛን ለመቆጣጠር ማቀዳቸውን አድንቀው «የፕሬዚደንቱን በድፍረት የተሞላ ዕቅድ በደስታ እንቀበላለን ፤ በየትኛውም ዓለም እንደሚሆነው የጋዛ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸዉ በነጻነት መውጣት እና መሰደድ ሊፈቀድላቸው ይገባል » ብለዋል።

ሚንስትሩ ፍልስጥኤማዉያኑ በየብስ ፣ በባህር አለያም በአየር እንደምርጫቸው ከጋዛ መውጣት እንዲችሉ አማራጮች ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

የአረብ እና የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራትን ጨምሮ በርካታ ሃገራት የፍልስጥኤማዉያኑን ከሃገራቸው እንዲሰደዱ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ሃሳብ ተቃዉመዋል።

የፍልስጥኤም አስተዳደር ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስ በበኩላቸው የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዕቅድ በይፋ ውድቅ ባደረጉበት መግለጫቸው ። «ህጋዊ የፍልስጥኤማዉያን መብቶች ለድርድር አይቀርቡም»… ሃሳቡም «ከባድ የመብት ጥሰት ነው » ብለውታል።

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ በበኩላቸው“የፍልስጤም ሕዝብ በገዛ ምድራቸው እንደሰው የመኖር የማይገሰስ መብቶች» እንዳላቸው አጽንዖት ሰጥተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *