ሊቨርፑል ለካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ደርሰዋል !

በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ሊቨርፑል ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ኮዲ ጋክፖ ፣ መሐመድ ሳላህ ፣ ስቦዝላይ እና ቫን ዳይክ አስቆጥረዋል።

ሊቨርፑል ቶተንሀምን በድምር ውጤት 4ለ1 በማሸነፍ ለካራባኦ ካፕ ፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

ሊቨርፑል ለካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ሲደርስ ይሄ ለ 15ተኛ ጊዜ ሲሆን በውድድሩም የዚን ያህል ጊዜ ለፍፃሜ  የደርሰ ክለብ የለም።

ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ  የፍፃሜው  ጨዋታ መጋቢት 7/2017 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *