ያለደረሰኝ ሲገበያዩ በነበሩ ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ  ከ2 መቶ 97 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል ተባለ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ዋና ሃላፊ አቶ ሰውነት አየለ፤ያለደረሰኝ ሲገበያዩ በነበሩ ነጋዴዎች ላይ፤ ተቋማቸዉ በወሰደዉ እርምጃ ከ2 መቶ 97 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ መንገድ የቁጥጥር ስራ በጥናት ላይ በመመስረት ተከናዉኗል ያሉት አቶ ሰዉነት፤ 671 ትላልቅ ድርጅቶች ላይ ምርመራ ተከናዉኖ 632 ድርጅቶች ፤ያለ ደረሰኝ ሲገበያዩ  አግኝተናቸዋል ብለዋል፡፡

አቶ ሰዉነት እነዚህ ድርጆት ላይ በተወሰደ እርምጃ  63 ሚሊዮን 2 መቶ ሺህ ብር ከቅጣት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

8 መቶ 39 የንግድ ተቋማት ተጠርጥረዉ ጉዳዮቻቸዉ በፍርድ ቤት የማጣራት ስራ እየተሰራባቸዉ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በፍርድ ቤት ተይዞ የማጣራት ስራ እየተካሄደባቸዉ  የሚገኙት  የድርጅቶቹ ባለቤቶች ቢቻ ሳይሆኑ በሽያጭ ባለሙያዎችም ላይ ነዉ ብለዉናል፡፡

በሺያጭ መሳሪያዎች በደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች ወይንም ነጋዴዎች  ላይ በተደረገ ድንገተኛ የቁጥጥር ስራም 3 ሺህ 2 መቶ 29 ያለደረሰኝ ሲገበያዩ ተገኝተዉ፤ 2መቶ 34 ሚሊዮን 50 ሺህ ብር እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

ዋና ሃላፊዉ በስድስት ወሩ ዉስጥ በተሰራ የቁጥጥር ስራ በሁለቱ ዘርፍ በአጠቃላይ ከ2 መቶ 97 ሚሊዮን ብር በላይ ከቅጣት መገኘቱንት ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ልኡል ወልዴ

ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *