በአዲ አባበ ባለፉት ስድስት ወራት 96 የእሳት አደጋዎች መድረሳቸውን እና አብዛኛዎቹም በኤሊክትሪክ ችግር መከሰታቸውን በምርመራዬ አረጋግጫሁ ብሏል የፌደራል ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች የደረሱ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል ።

በዚም መሰረት በከፍተኛ የአደጋ መንስኤነት የኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር አንዱ ሲሆን 50 የሚሆኑ የቃጠሎ አደጋዎች መድረሳቸውን ገልጻል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤም በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር የተከሰተ አደጋ መሆኑን በፎረንሲክ ምርመራ ማጣራት ችያለሁ ብሏል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ።

በሌሎች የአደጋ መንስኤነት በመካኒካል ችግር ምክንያት የደረሰ 11 ፤ ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 10 ፤ በቸልተኝነት የደረሰ 17 እና በሌሎች ምክንያቶች የደረሰ 15 ቃጠሎ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤት፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1965 ንግድ ቤቶች፣ በስድስት ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የስድስት ወር ሪፖርት እንደሚያመላክት ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኅብረተሰቡ ቃጠሎ ከደረሰ በኋላ ማስረጃዎች ሳይነካኩ መጠበቅና ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት እንዲሁም የቃጠሎ መንስኤዎች በሙያዊ ምርመራ እስካልተረጋገጡ ድረስ አስተያየት መስጠትና መፈረጅ ፍትሕን እንደሚያዛባ ተገንዝቦ ለፍትሕ መረጋገጥ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *