ዶዳይ የኤሌከትሮኒክ ሞተር አምራችና አከፋፋይ ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ280 በላይ አባላት ያሉት የኤሌትሪክ ሞተር ብስክሌት ባለቤቶች ማኅበርን አቋቁሟል ።
የዶዳይ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዩማ ሳሳኪ፤ድርጅቱ ለመጀመሪያዎቹ 250 ደንበኞች የታርጋ ወጪን በመሸፈን አዲስ ጅምሮ መዘርጋታቸውን ተናግረዋል ።
ስራ አስፈፃሚው ይህ እርምጃ የኤሌክትሮኒክ ሞተርባይክ ተጠቃሚዎች በኢትዮጵያ የበለጠ ተደራሽ በማድረግና በተመጠጠኝ ዋጋ በማቅርብ እድል ተፈጥሯልም ብለዋል።
የኤሌትሪክ ሞተር ብስክሌት ባለቤቶች ማኅበር ም/ፕሬዚዳንት ህሊና ለገሰ፤ማህበሩ መቋቋሙ ሞተረኞች የሚገጥማቸውን ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል ብለዋል።
መሀበሩ በሚያደርገው ዘላቂ የትራንስፖርት ሽግግር፣ የባለቤትነት ልምድን የበለጠ ለማሳደግና አባላቱ ተገቢውን የከተማ ትራፊክ ደንብ ተከትለው አገልግሎት እንዲያገኙም ሆነ እንዲሰጡ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።
ድርጅቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ”850 በላይ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶችን መሸጡን ገልጿል።
ድርጅቱ በአሁን ሰዓት የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎችና የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ላይ መሆኑን ሰምተናል።
ዶዳይ በኢትዮጵያ ቀዳሚ የኤሌክትሪክ ኩባንያ ሲሆን አዳዲስና ዘላቂ የትራንስፖርት መፍትሄዎችን በማቅረብ፤ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ በኢትዮጵያ የከተማን እንቅስቃሴን ለመቀየር እየሰራ ይገኛልም ተብሏል።
ልኡል ወልዴ
የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም
